Song Lyrics

ተመችቶኝ ነው

Meskerem Getu
Eketelihalew
አዝ፦ ተመችቶኝ ነው ጌታ ፍቅርህ ተመችቶኝ ነው (4x) ከአንተ ጋራ መዋል ማደር ከአንተ ጋራ (4x) ሲከፋኝ ስጨነቅ ሆድ ሲብሰኝ ከጐኔ ሲጠፋ የሚረዳኝ ብቻዬን ያልተውከኝ ምድረ በዳ አለሁኝ የምትል ለተጐዳ አዝ፦ ከአንተ ጋራ መዋል ማደር ከአንተ ጋራ (4x) ከወረት ያልሆነ ታላቅ ፍቅርህ ሀዘኔን የሚያልፍ መፅናናትህ እምባዬን ያበሰከው ደጋፊዬ ስተክዝ ሆንክልኝ መፅናኛዬ አዝ፦ ከአንተ ጋራ መዋል ማደር ከአንተ ጋራ (4x) አትከዳኝ አትለወጥ በሁኔታ አተወኝ ስደክም ስበረታ ፍቅርህ የፍቅሮች ሁሉ አውራ ዘለዓለም የሚቀጥል እያበራ አዝ፦ ተመችቶኝ ነው ጌታ ፍቅር ተመችቶኝ ነው (4x) ከአንተ ጋራ መዋል ማደሩ ከአንተ ጋራ (2x) ሲከፋኝ ስጨነቅ ሆድ ሲብሰኝ (ከአንተ ጋራ) ከጐኔ ሲጠፋ የሚረዳኝ (ከአንተ ጋራ) ብቻዬን ያልተውከኝ ምድረ በዳ (ከአንተ ጋራ) አለሁኝ የምትል ለተጐዳ (ከአንተ ጋራ) (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection