የፍቅሬ መሃል ነህ የመወደዴም ቅኔ አንዳች አልቆጥብም አሰማለሁ እኔ የመስዋዕቴን በኩራት የፍቅሬን ፍታ አዘጋጅቻለሁ ላፈሰው ለጌታ (2x) አዝ፦ ለእኔስ የዘውትር ጥማቴ መሻት የቀን የሌሊት ናፍቆቴ የአንተን ክብር ማየቴ በዕድሜ በሰጠኸኝ ዘመኔ በዕድሜ በሰጠኸኝ ዘመኔ (2x) የወርቅ ፍልቃቂ የክብር ሙዳዬ በሞገስ ያጌጥከው መጐናፀፊያዬ የፊቴ መድኃኒት የርስቴ ዕድል ፈንታ ከአንተ ሌላ አላውቅም የልጅ ልጅ ደስታ (2x) አዝ፦ ለእኔስ የዘውትር ጥማቴ መሻት የቀን የሌሊት ናፍቆቴ የአንተን ክብር ማየቴ በዕድሜ በሰጠኸኝ ዘመኔ (2x) ከደስታዬ በላይ አንተን ወድጃለሁ ፅድቅን መከታተል ተለማምጃለሁ ሌላ ሌላውማ መች ልቤ ደረሰ የአንተ ዘይት ብቻ ሕይወቴን አራሰ ሌላ ሌላውማ መች ልቤ ደረሰ የአንተ ቅባት ብቻ አንጀቴን አራሰ አዝ፦ ለእኔስ የዘውትር ጥማቴ መሻት የቀን የሌሊት ናፍቆቴ የአንተን ክብር ማየቴ በዕድሜ በሰጠኸኝ ዘመኔ (2x)