Song Lyrics

መነሻህ ከፍታ

Lealem (Lali) Tilahun
Yenardos Shitoye
ከሰማሁትና ይበልጣል ልዑል ሆይ መዓዛህ ያውዳል ከመንግስትህ ህግ ሁኔታ መች ተነገረ ለአንተ ጌታ (2x) ከጥበብህ ህግ ሁኔታ መች ተዘመረ ለአንተ ጌታ መች ተዘመረ ለአንተ ጌታ (2x) አዝ፦ መነሻህ ከፍታ መድረሻህ ከፍታማ ጅማሬህ ከፍታ ፍፃሜህ ከፍታማ ዙፋንህን ዘርግትህ ከፍ ባለው ቦታ ፀንተህ ትኖራለህ የእኔ ጌታ (2x) ፀንተህ ትኖራለህ የእኔ ጌታ (2x) የምድር ጠቢባን ሊቃውንቱ የፍጥረትን ጥያቄ መች ፈቱ የጥበብ የእውቀት የሥልጣኔ መጀመሪያው አንተው ነህ መድህኔ መጨረሻው አንተው ነህ መድህኔ (2x) ሊቃውንቱ እንዲህ ይበሉ ኃያላኑ እንዲህ ይበሉ ጠቢባኑ እንዲህ ይበሉ ሠራዊቱ እንዲህ ይበሉ ኤልሻዳይ እግዚአብሔር ብቻ ሁሉን ቻይ እግዚያብሔር ብቻ ኤሎሂም እግዚአብሔር ብቻ አዶናይ እግዚአብሔር ብቻ (2x) እግዚአብሔር ብቻ (8x) ከምድር ዳርቻ እስከ ጫፍ ከሠማይም አፅናፍ እስከ አፅናፍ ከትውልድ የትውልዶች መካከል መች ተገኘ አንተን የሚስተካከል መች ተገኘ አንተን የሚስተካከል (2x) አዝ፦ መነሻህ ከፍታ መድረሻህ ከፍታማ ጅማሬህ ከፍታ ፍፃሜህ ከፍታማ ዙፋንህን ዘርግትህ ከፍ ባለው ቦታ ፀንተህ ትኖራለህ የእኔ ጌታ (2x) ፀንተህ ትኖራለህ የእኔ ጌታ (2x) ከፍ ከፍ (2x) ብለህ ከፍ ከፍ ብለህ የክብር የምሥጋናን ዘውድ ተጭነህ በማይናወጠው ፅኑ መንግስትህ ያለ ተቀናቃኝ ትገዛናለህ (2x) ኤልሻዳይ እግዚአብሔር ብቻ ሁሉን ቻይ እግዚያብሔር ብቻ ኤሎሂም እግዚአብሔር ብቻ አዶናይ እግዚአብሔር ብቻ (2x) እግዚአብሔር ብቻ (፲6x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection