አዝ፦ አመልክሃለሁ ጌታ እገዛልሃለሁ በደስታ (2x) ብዙ ምርኮን እንዳገኘ ሰው እኔም በአንተ ደስ ተሰኘሁ (2x) እወድሃለሁ ብልህ መች ይገልፅልኛል አፈቅርሃለሁ ብልህ መች ይገልፅልኛል ምድራዊው ቃል ሁሉ እጅግ አንሶብኛል ግን ደግነቱ አንተ መች ቃል ትቆጥራለህ ይልቅ የውስጥ የልብን መመዝን ታዋቃለህ (2x) እንደ ወንዝ እንደ ጅረት እንደሚጠጣ ገነት (2x) የፅድቅ ብዛት የአንተ ፀጋ የተጠማችን ነፍስ የሚያረካ (2x) የሕይወትን ጥም የሚያረካ (4x) አዝ፦ አመልክሃለሁ ጌታ እገዛልሃለሁ በደስታ (2x) ብዙ ምርኮን እንዳገኘ ሰው እኔም በአንተ ደስ ተሰኘሁ (2x) የምህረትህ ጥገኛ የፍቅርህ ድግሞ እስረኛ (2x) ከአንተ ውጭ የለኝም ማንነት ላፍሰው ልቤን በአንተ ፊት ከአንተ ውጭ የለኝም ማንነት ላፍሰው ልቤን በአንተ ፊት (6x)