Song Lyrics

የናርዶስ ሽቶዬ

Lealem (Lali) Tilahun
Yenardos Shitoye
የናርዶስ ሽቶዬ የአልባስጥሮስ መጓደጃዬ ውድ ኢየሱስ ልቤ ከልብህ ጋር ተቆራኝቶ መኖር ወደደ አንተን አግኝቶ (2x) አንተን አግኝቶ (4x) አዝ፦ ቅዱሱ እግዚአብሔር የማውቀህ ከልጅነቴ ንጉሡ እግዚአብሔር የምሻህ ከልጅነቴ እርስቴም ተድላዬም ጥጋቤም አንተ ነህ ማር እና ወተቴ (5x) የቆላ አበባ ፅጌረዳዬ የእግዚአብሔር ልጅ ውሎ መግቢያዬ በማሰማሪያህ በታዛ ሥር አንተን ሳመልክህ ውዬ ልደር (5x) ውዬ ልደር (4x) መጣሁኝ ወዳሳየኸኝ ውብ ሥፍራ አየሁ የግርማህን ፀዳል ሲያበራ ወዳጄ ለመሆኑ ሰው አወቀህ ወይ ቁንጅናህ ለሀገር የሚተርፍ አይደል ወይ (3x) አዝ፦ ቅዱሱ እግዚአብሔር የማውቀህ ከልጅነቴ ንጉሡ እግዚአብሔር የምሻህ ከልጅነቴ እርስቴም ተድላዬም ጥጋቤም አንተ ነህ ማር እና ወተቴ (5x) ልቤ መልካምን ቅኔ አፈለቀ ንጉሡን ጌታ እያደነቀ ውበቱ ከአምራል ከሰው ይልቅ የእኔማ ኢየሱስ ከብርቅም ብርቅ (4x) አዝ፦ ቅዱሱ እግዚአብሔር የማውቀህ ከልጅነቴ ንጉሡ እግዚአብሔር የምሻህ ከልጅነቴ እርስቴም ተድላዬም ጥጋቤም አንተ ነህ ማር እና ወተቴ (9x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection