Song Lyrics

ኢየሱሴ

Lealem (Lali) Tilahun
Yenardos Shitoye
በምሥጋና አከብርሃለሁ በዝማሬ አደንቅሃለሁ (2x) ኢየሱሴ ወድጄሃለሁ ኢየሱሴ አፍቅሬሃለሁ አዝ፦ ኢየሱሴ (2x) መታመኛዋ ለነፍሴ ኢየሱሴ (2x) መደገፊያዋ ለነፍሴ (2x) ልባርክ ነው ብለህ ሳታማክራቸው ላስደንቅ ነው ብለህ ሳታማክራቸው (2x) ፍፁም ሳይጠብቁ ፍንጭን ሳትሰጣቸው አቤት ጠላቶቼን ጉድ አደረካችው (2x) ጉድ አደረካቸው (4x) አዝ፦ ኢየሱሴ (2x) መታመኛዋ ለነፍሴ ኢየሱሴ (2x) መደገፊያዋ ለነፍሴ (2x) ከፊተኛው ይልቅ እንዲሻል ኋለኛው ተናገረህ የለም ዎይ ጌታ ጥበበኛው (2x) አዲስ የወይን ጠጅ በአዲስ አቁማዳ ታናኳዬን ሞላኸው በበረከት ናዳ (2x) በበረከት ናዳ (4x) አዝ፦ ኢየሱሴ (2x) መታመኛዋ ለነፍሴ ኢየሱሴ (2x) መደገፊያዋ ለነፍሴ (2x) ቀንበር የሚሰብር የቅባት ውፍረት ሕይወትን የሚያድስ የፀጋ ሙላት (2x) የበረከት ዝናብ ውሽንፍር ሲመጣ አልዋለ አላደረም ፋሬስ ጥሶ ወጣ (2x) ፋሬስ ጥሶ ወጣ (4x) አዝ፦ ኢየሱሴ (2x) መታመኛዋ ለነፍሴ ኢየሱሴ (2x) መደገፊያዋ ለነፍሴ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection