ከዕንቁና ከብዙ ወርቅ የምትበልጥብኝ የእኔ እፁብ ድንቅ እህል ውኃዬ የእኔ ዕድል ፈንታ መጓደጃዬ እርሱ ነው ጌታ (2x) አዝ፦ እራሱ ነው ጌታ እራሱ ነው አሃ እራሱ ነው ጌታ እራሱ ነው (2x) የሞገስ አክሊል የክብር ሹመቴ የማዕረግ ዘንግ ሆነህ ለሕይወቴ ገመድ ባማረ ሥፍራ ወድቃለች በአንተ በአምላኬ ርስቴም ተዋበች የእኔ ትርጉም በረከት ማለት የእኔ ትርጉም አሃ የሕይወት ምንነት የእኔ ትርጉም ባለ ጠግነት የእኔ ትርጉም አሃ የኑሮ ስኬት ከምንም ነገር ሁሉ በላይ እራሱ እግዚአብሔር አይደለም ዎይ (2x) አዝ፦ እራሱ ነው ጌታ እራሱ ነው አሃ እራሱ ነው ጌታ እራሱ ነው (2x) በእጁ መነካት ተነክቼአለሁ የክብሩን ውበት በዓይኔ አይቻለህ በደረስኩበት በሁሉም ቦታ እናገራለሁ ስለዚህ ጌታ (2x) የእኔ ትርጉም በረከት ማለት የእኔ ትርጉም አሃ የሕይወት ምንነት የእኔ ትርጉም ባለ ጠግነት የእኔ ትርጉም አሃ የኑሮ ስኬት ከምንም ነገር ሁሉ በላይ እራሱ እግዚአብሔር አይደለም ዎይ (2x) አዝ፦ እራሱ ነው ጌታ እራሱ ነው አሃ እራሱ ነው ጌታ እራሱ ነው (4x)