Song Lyrics

የቀደስካቸው

Lealem (Lali) Tilahun
Yenardos Shitoye
አዝ፦ የቀደስካቸው እጆቼን አንስቼ ማምለክ ስጀምር ዓይኖቼን ወደላይ አቅንቼ (2x) ህዋሳቶቼ አካላቶቼ አንተን ይሉኛል አጥንቶቼ ህዋሳቶቼ አካላቶቼ አንተን ይሉኛል አጥንቶቼ ለሰው ልጅ ልማድነቱ ክብርና ሞገስ በሕይወቱ ለስብዕናውም ትርጉም ከአንተ ውጭ አልተገኘም ከአንተ ሌላ የለም የለም አማራጭ የሌለህ ምርጫዬ የሕይወቴ ገነት ተድላዬ ያለ አንዳች ቅንጣት ቅሬታ ፈቅጄ የማመልክህ በደስታ እድል ፈንታዬ የእኔ ጌታ አዝ፦ የቀደስካቸው እጆቼን አንስቼ ማምለክ ስጀምር ዓይኖቼን ወደላይ አቅንቼ (2x) ህዋሳቶቼ አካላቶቼ አንተን ይሉኛል አጥንቶቼ ህዋሳቶቼ አካላቶቼ አንተን ይሉኛል አጥንቶቼ አጥንት ከአጥንት ሳይዋደድ ሳልሰራ በእናቴ ሆድ ቀኖቼን ጽፈህ በመጽሐፍ እንደ ፈቃድህ እንደ ሀሳብህ አራመድከኝ በትንቢት ቃልህ አጋጣሚ አይደል ዎይ በድንገት የሆንኩትን ሁሉ የሆንኩት የሕይወቴን አቅጣጫ ቀያሪ ፈላጭ ቆራጭ ሆኖ አንተ ነህ የልቤ መርማሬ አዝ፦ የቀደስካቸው እጆቼን አንስቼ ማምለክ ስጀምር ዓይኖቼን ወደላይ አቅንቼ (2x) ህዋሳቶቼ አካላቶቼ አንተን ይሉኛል አጥንቶቼ ህዋሳቶቼ አካላቶቼ አንተን ይሉኛል አጥንቶቼ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection