ከፍ አድርጌ መለከቴን እነፋለሁ ምሥጋናዬን አውጃለሁ (2x) ከፍጥረታት ጋር ተባብሬ ያለ የሌለኝን ጭምሬ እቀኛለሁ ለንጉሤ ጌታ መጥቷል በመቅደሴ (2x) መድኃኒዓለም እውነትም አንተ እውነትም መድኃኒት ነህ አባትህ ይህንን አውቆ ኢየሱስ ብሎህ ጠራህ የባህሩ ምሳሌ የክብሩ ነፀብራቁ ነህ የእኔንም ሕይወት ያደመቅህ የደስታዬ ፍፃሜው ነህ ጌታዬ ዕድል ፈንታዬ የዘላለም መኖሪያዬ አምላክ የምለው አንተን ነው ምሥጋናዬን/አምልኮዬን ተቀበለው ወዳጅ የምለው አንተን ነው ምሥጋናዬን ተቀበለው (2x) ረዳት የምለው አንተን ነው ምሥጋናዬን ተቀበለው እያደር እያደር ዛሬማ እያደረ ይገረመኝ ጀመረ የመዳኔ ነገር እያደር እያደር ዛሬማ እያደረ ይደንቀኝ ጀመረ የመዳኔ ነገር ለካ ድኛለሁ ከሞት አምልጬ የጠላቶችን እራስ ረግጬ (2x) የሚያስደንቅ ነው መዳኔ እንደበራለኝ ለእኔ ኢየሱሴ ሆነልኝ ማንም የማይወስድብኝ መዳኔ ድንቅ ነው መዳኔ ልዩ ነው (3x) ከፍ አድርጌ መለከቴን እነፋለሁ ምሥጋናዬን አውጃለሁ (2x) ከፍጥረታት ጋር ተባብሬ ያለ የሌለኝን ጭምሬ እቀኛለሁ ለንጉሤ ጌታ መጥቷል በመቅደሴ (2x)