አዝ:- ተናግሬም አልጨርሰው ጌታ ለእኔ ያደረገው (2x) ልነሳና እስኪ ልቀኝ ለእርሱ ሚሆን ቋንቋ ቢገኝ (2x) ዝም ልል አልችልም ፍቅርህ ዝም አያሰኝም ጥበቃህና ምሕረትህ ከአይምሮ በላይ ነው መውደድህ (2x) ለመጠሩት ሁሉ ባለ ጠጋ ከወንድም አብልጦ የሚጠጋ ከማንስ ጋር ከቶ ይወዳደራል ከአእላፋት ይልቅ እርሱ/ጌታ ይበልጣል (2x) ከቤቱ በረከት የሚያጠግበን የዘላለም አባት የማይተወን ጎልማስነታችን ደስ የምያሰኛት ውዱ የእኛ ጌታ የእኛ መድሃኒት (2x)