Song Lyrics

ዙፋንህ የዘላለም ነው

Lealem (Lali) Tilahun
Hayilin Yemiyastatikegn
አመታቶችህ ከቶ አያልቁም የዘመንህ ቁጥር አይመረመርም አልፋ ኦሜጋ ፊተኛ ኋለኛ የእግዚአብሔር ልጅ ንጉስ ነህ ለእኛ አዝ:- ዙፋንህ የዘላለም ነው መንግሥትህ ማንም አይሽረው አንተ ግን አንተው ነህ ዘላለም ኢየሱስ የሚመስልህ የለም (2x) ስልጣን የአንተ ነው መንግስት የአንተ ነው አምላክና አባት አዳኝ የሆንከው የሲኦልን ቁልፍ በእጅህ ይዘሃል ጻድቅ ፈራጅ ነህ ክብር ይገባሃል ከጥንት ጀምሮ ምድርን መሰረትክ በእጆች ሥራ ሰማይን ሰራህ የፍጥረት ገዢ አምላክ አንተ ነህ ሁሉም ያልፋሉ አንተ ግን ያው ነው ከስሞች በላይ ታላቅ ስም ይዘህ በአባትህ ቀኝ በክብር ያለህ የሁሉ ጌታ የሁሉ ንጉስ የእኛም መድሃኒት አንተ ነህ ኢየሱስ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection