ፅድቅና መንግሥትህ እንደምን ያምራሉ ከአንተ ወድያ ሕይወት ለምን ያሰኛሉ የአባትነትህ ፍቅርህ በኢየሱስ ያየነው ማርኮ አስቀርቶናል ኑሮዋችን የአንተ ነው (2x) አዝ:- ክቡርና ቅዱስ ኃያል ልዑል አባት እግዚአብሔር ከአንተ በቀር ማንም የለም አልነበረም ደግሞ አይኖርም (2x) ሥራህን እያየን እናደንቅሀለን ሁልጊዜ ፍቅርህን ጌታ እናስባለን መንፈስና ሥጋ ነፍሳችን ተስማምተው ያመሰግኑሃል ክበር ጌታ ብለው (2x) ውለታህ አለብን ከልብ የማይጠፋ እኛን የረዳኸን ኢየሱስ ክብርህ ይስፋ ከቶ ምን አለና ለእኛ ያላደረከው መድኃኒታችን ሆይ ክብራችን ከአንተ ነው (2x) ከፀሐይ ሰባት እጅ ድምቀህ ትታያለህ ሁለንተናህ ውብ ነው ምንም አልጐደለህ ለግርማዊነትህ ክብር እንሰግዳለን ልዑል ሆይ ለሥምህ እንዘምራለን (2x) ከአንተ በቀር ማንም የለም አልነበረም ደግሞ አይኖርም (2x)