Song Lyrics

መዳኔ ሲገርመኝ

Lealem (Lali) Tilahun
Hayilin Yemiyastatikegn
መዳኔ ሲገርመኝ አይኔ መከፈቱ ደግሞ ታምራትህ በዛ በየእለቱ (2x) አንተን አመስግኜ ማቋረጥ አልችልም ውስጤ የገባው ፍቅርህ ዝም አያሰኘኝም ዝም አያሰኘኝም (2x) አዝ:- ዓይኖቼንም እያበራህ ጉልበቴንም እያጸናህ ወደ ፊት እያራመድከኝ በድል ላይ ድልን ሰጠኅኝ በእውነት አንተ ጌታ ነህ ምስጋናዬም ይድረስህ በእውነት አንተ ንጉስ ነህ አምልኮዬም ይድረስህ በእውነት አንተ ጌታ ነህ ምስጋናዬም ይድረስህ በእውነት አንተ ንጉስ ነህ አምልኮዬም ይድረስህ (2x) መዘመር ለአንተ ነው ማምለክም አንተን ድንቅን እየሰራህ ለምታኖረን (2x) እንዲያው ክበር እንጂ ሌላ ምን ይባላል ጌታ ያንተ ፍቅር ክመታወቅ ያልፋል ክመታወቅ ያልፋል (2x) አንተው በሰጠህኝ በዚች አንደበቴ እባርክሃለሁ ክበር መድኃኒቴ (2x) ከልብ የፈለቀ የምስጋና ዜማ ይሄው አምጥቻለሁ በፊትህ ላሰማ በፊትህ ላሰማ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection