አዝ:- ለእኔስ ከአንተ ሚበልጥ ወዳጅ የለኝም ፍቅርህ ዛሬም ትኩስ ነው በልቤ ከቶ አይበርድም (2x) በመንፈስ ቅዱስ በልቤ የፈሰሰው አቤቱ ፍቅርህ መተኪያ የለው (2x) ብዙ ውሆች እንኩዋን ሊያጠፉት አልቻሉም ግሩም ነው ግሩም ነው ፍቅርህ አይነገርም የብርሃን አባት የእኔ መመኪያ ፍቅርህ ሁሌ አዲስ ነው ከልቤ ማይጠፋ (2x) አንተን አንተን እንጂ ማንንም አልልም አምላኬ ጌታዬ እኔስ አልጠግብህም የነፍሴ ጥጋብ የሕይወቴ አለኝታ መጠጊያዬ ነህ ብሩኩ ጌታ (2x) ነፍሴን በምሕረትህ አድነሃልና የመድህንቴ አምላክ ይድረስህ ምስጋና