እወድሃለሁ አጅግ አብዝቼ ከልቤ ጋራ እጄን አንስቼ በምን ቋንቋ ነው ከቶ ምገልጸው የልቤ አምላክ ሆይ ፍቅርህ ብርቱ ነው (2x) አዝ፦ ቃላት ባገኘሁና ባወራው የአንተን ምስጋና የልቤ በደረሰልኝ አምላኬ አንተው ከብረህልኝ የሚያስፈልገኝ አንድ ነገር እርሱም አንተው ነህ ጌታ እግዚአብሔር አንተን ካገኘሁ ጠግቤ አድራለሁ ስለዚህ አምላኬ እወድሃለሁ (2x) መላ እኔነቴ አንተን ይወዳል በቀን በለሊት ልቤ ያስብሃል ያላንተ መኖር አይሆንልኝም ሕይወቴ አንተ ነህ ሌላም የለኝም (2x) አዝ፦ ቃላት ባገኘሁና ባወራው የአንተን ምስጋና የልቤ በደረሰልኝ አምላኬ አንተው ከብረህልኝ የእግዚአብሔር ልጅ መድህኔ ሕይወቴ ነህ አንተ ለእኔ (2x) ሕይወት ተገለጠ እኔም አይቻለሁ ጌታ ቸር መሆኑን ቀምሼ አውቄያለሁ እግዚአብሔር አምላክ ነው እኔም በርቶልኛል ታዲያ ከእርሱ ፍቅር ማንስ ይለየኛል ሰው አንተን ካገኘ ምን ያስፈልገዋል እፎይ ብሎ አርፎ ተደላድሎ ይኖራል ፍቅርህ የሚያጠገብ ልብን የሚያረካ የመኖር ትርጉሙ ጌታ አንተ ነህ ለካ