አዝ:- ሁሉን አድርገህልኛል የቀረብኝም የለም ሌላ ምልህ ባይኖረኝ እወድሃለሁ እኔም ሌላ ምልህ ባይኖረኝ እወድሃለሁ እኔም (2x) የሰማይን ፀጋ የምድርን በረከት በሌላ እኮ አይደለም ባንተ ነው ያገኘሁት ጽድቅና ሰላምን የመንፈስን ደስታ አጎናጽፈኅኛል የሰራዊት ጌታ (2x) አዝ:- ሁሉን አድርገህልኛል የቀረብኝም የለም ሌላ ምልህ ባይኖረኝ እወድሃለሁ እኔም ሌላ ምልህ ባይኖረኝ እወድሃለሁ እኔም (2x) ምን ያጠያይቃል መልካምነትህ ለኔስ ጌታ ኢየሱስ በረከቴ ነህ መወደድ ስይንስህ ነው መች ይበዛብሃል እንኳን እኔነቴ ዘሬ የገዛልሃል እየዋለ እያደር ታምራትህ በዛ የነገስታት ንጉስ የጌቶቹ ጌታ (2x) ምን እንልሃለን ማዳንህን እያየን በምስጋና በላይ ምስጋናን እንሰዋለን ምን እንልሃለን ምሕረትህን እያየን በክብርም በላይ ክብርን እንሰጣለን መልካምን ማድረግ ማይታክትህ አቤት እግዚአብሔር ቸርነትህ አሃሃ ትላንት ያረከው ሳይበቃህ ዛሬም ደገምከኝ አብዝተህ (2x) በክብር ላይ ሌላ ክብር በክብር ላይ አሃ ቆርጫለሁ ለመጨመር ከዚያም በላይ አንደበቴን በምስጋና እየከፈትኩ ኦሆ ለድል ጌታ የድል ዜማን አመጣለሁ እየዋለ እያደር ታምራትህ በዛ የነገስታት ንጉስ የጌቶቹ ጌታ (2x) ምን እንልሃለን ማዳንህን እያየን በምስጋና በላይ ምስጋናን እንሰዋለን ምን እንልሃለን ምሕረትህን እያየን በክብርም በላይ ክብርን እንሰጣለን ተራሮችንም ትክክል አደረክና እግዚአብሔር አሃ የነሃሱን ደጆች ሰባብረህ እኔን ለክብር አበቃህ (2x) በክብር ላይ ሌላ ክብር በክብር ላይ አሃ ቆርጫለሁ ለመጨመር ከዚያም በላይ አንደበቴን በምስጋና እየከፈትኩ ኦሆ ለድል ጌታ የድል ዜማን አመጣለሁ አምላኬ መታመኛዬ ነው ጌታዬ ንጉሴ መደገፊያዬ ነው አምባዬ (2x)