Song Lyrics

መዝሙር አልቀይርም

Kefa Mideksa
Hulum Yisma
መዝሙር አልቀይርም ቃሌ ቃል ነውና መልካምነትህን ዘምሬይለሁና ሲሆን ተደስቼ ሳይሆን ተከፍቼ አላማህም ጌታ እኔ አፌን ሞልቼ ዛሬም እላለሁ እንዲህ እላለሁ የሕይወት ራስ ነህ ንጉሤ አልሃለሁ (2x) የሕይወት ራስ ነህ ራስ ለቤቴ ተመስገንልኝ ኢየሱስ አባቴ (2x) ያልደምከምኩበትን ሕይወት ሰጥተኸኛል እንዳገለግልህ እድል ሰጥተኸኛል እርግማኔን ባርኮት አርገህ የቀየርክ ፍጻሜዬ በሃዘን እንዳይዘጋ ነው አልቀለለብኝም ክቡር ነው መዳኔ ምሥጋናን ባበዛ ሲያንስብኝ ነው እኔ የጥረቴ ድካም ሳታደርግብኝ እንዲሁ በፀጋህ ኢየሱስ አዳንከኝ አዳንከኝ ኦ የማንም እጅ የለበትም ስለመዳኔ ስለመትረፈ ተመስገንልኝ አባዬ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection