Song Lyrics

አንድ ወዳጅ

Kefa Mideksa
Hulu Beju New
አንድ ወዳጅ (2x) አለኝ ለእኔ የሞተልኝ (4x) ቅጣቴን የተቀጣህልኝ አበሳዬን ከእኔ ወሰድክልኝ (2x) ጌታ ተባረክልኝ ኢየሱስ ተባረክልኝ ጌታ ተባረክልኝ (2x) ሙግቴን ተሟግቶ አሸንፎልኛል ጠላቴ እንዳይከሰኝ ነጻ ነህ ብሎኛል ይህን ወዳጄን ወዳጄ ነህ ያልኩት ከማንም አብልጬ በልቤ የሾምኩት አዝ፦ ለእኔ መልካም በማድረግ የታወቀው መልካም በማድረግ የታወቀው ለእኔ መልካም በማሰብ የታወቀው መልካም በማሰብ የታወቀው እርሱ እግዚአብሔር ነው እግዚአብሔር ነው (2x) እርሱ ጌታዬ ነው ጌታዬ ነው (2x) በምክሩ ግሩም ነው ነፍስን ይመልሳል ከወዳጅ አብልጦ ወደ ልብ ይጠጋል ደብቆ የያዘኝ እንዳልሆን የሌላ የቅርቤ የምለው ማነው ከእርሱ ሌላ አዝ፦ ለእኔ መልካም በማድረግ የታወቀው መልካም በማድረግ የታወቀው ለእኔ መልካም በማሰብ የታወቀው መልካም በማሰብ የታወቀው እርሱ እግዚአብሔር ነው እግዚአብሔር ነው (2x) እርሱ ጌታዬ ነው ጌታዬ ነው (2x
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection