Song Lyrics

የሚያውቅልኝ ጌታ

Kefa Mideksa
Hulu Beju New
የሚያውቅልኝ ጌታ ያውቅልኛልና ሰው አልደገፍም ይሰበራልና ዛሬ ታይቶ ነገ በሚጠፋው ነገር ልቤን በዚያ አልጥልም አለልኝ እግዚአብሔር (2x) አለልኝ እግዚአብሔር (4x) አለልኝ አለልኝ የሚያስብልኝ (2x) የበላይ ነህ ጌታ የሁሉ በላይ እኩያ የሌለህ በምድር በሰማይ (2x) አምላክ አለኝና ሁሉን በእጁ የያዘ ሥሙም ድንቅ መካር ኃያል የተባለ ሰማይና ምድርን በቃሉ እንዳፀና እርሱን ባይሁ ጊዜ እኔም ልቤ ፀና (5x) ግራ አይገባኝም ነገን አስቤ ለወደፊቱ የታመንኩበት ሁሉ በእጁ ነው ሁሉ በደጁ የእንቆቅልሽ ሁሉ መፍቻ ቁልፍ ያለው የይሁዳ አንበሳ ከእኔ ጋራ ነው እንዳለው ነው እንደ ቃሉ ሁሉ በእጁ ሁሉ በደጁ እንዳለው ነው (እንዳለው ነው) እንደ ቃሉ (እንደ ቃሉ) ሁሉ በእጁ (ሁሉ በእጁ) ሁሉ በደጁ (ሁሉ በደጁ) (2x) የበላይ ነህ ጌታ የሁሉ በላይ እኩያ የሌለህ በምድር በሰማይ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection