Song Lyrics

አይረሳኝም

Kefa Mideksa
Hulu Beju New
እኔስ አልረሳሁም ያደረክልኝን ከጨለማ አውጥተህ ቀን ያወጣህልኝ (2x) ምስኪኑን ከጉድፍ ከአመድ አንስተኸው ከታላላቆች ጋር ስፍራ እንደሰጠኸኝ (2x) አይረሳኝም የእኔ ጌታ ያረክልኝ ብዙ ውለታ አይረሳኝም የእኔ ጌታ ስለእኔ ተንገላታህ አይረሳኝም የእኔ ጌታ ያረክልኝ ብዙ ውለታ አይረሳኝም የእኔ ጌታ የሆንክልኝ በጐልጐታ መቆም መቀመጤን በፊትህ አድርገህ ክፉ አንዳይነካኝ በዙሪያዬ ሆነህ (2x) የአመጽ ፈሳሽ አልፎ ቀን ወጣልኝ ለእኔ ምክንያቱ አንተ ነህ ጌታ ለመዳኔ (2x) የመኖሬ ምክንያቱ አንተ ነህ (2x) የመክበሬ ምክንያቱ አንተ ነህ (2x) የመቆሜ ምክንያቱ አንተ ነህ (4x) የተቆረጠና የአለቀውን ነገሬን ቀጥለህልኛል አይተህ መቸገሬን (2x) ብቻህን ያለአጋዥ የረዳኸን ጌታ ዘምረ ያሰኘኛል በዝቶ የአንተ ውለታ (2x) የመኖሬ ምክንያቱ አንተ ነህ (2x) የመክበሬ ምክንያቱ አንተ ነህ (2x) የመቆሜ ምክንያቱ አንተ ነህ (4x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection