Song Lyrics

ኢየሱስ ነው ጌታ

Kefa Mideksa
Hulu Beju New
አምልኮ (3x) ይለኛል ዛሬ ደግሞ መንፈስህ በእጥፍ አግኝቶኛል በል ዘምር (3x) ይለኛል የሚወደኝ ጌታ ምህረት አድርጐልኛል ጠላት በዙሪያዬ መርዶ ሲያረዳኝ የጌታዬ ሰላም ከላይ ሲያገኘኝ አስባለኝ ተባረክ ጌታዬ ተባረክ ተባረክ ኢየሱስ ተባረክ (2x) በሰማይ በምድር አሃ አለሁ የሚል ጠፍቶ ጀግና የተባል አሃ ሁሉ አንገቱን ደፍቶ መጽሐፉን ወስዶ ማኅተሙን የፈታ የይሁዳ አንበሳ ኢየሱስ ነው ጌታ ኢየሱስ ኢየሱስ ነው ጌታ (2x) ጌታዬ አንተ እኮ ነህ ጌታ (2x) ከአንተ በላይ ጌታ ከአንተ በላይ ንጉሥ በላዬ አልሾምኩም የናዝሬቱ ኢየሱስ ከሥም ሁሉ በላይ ሥም ያለህ አንተ ነህ በፍጥረት አንደበት ትመሰገናለህ ጌታዬ ትመሰገናለህ (2x) ሁልጊዜ ትመሰገናለህ (2x) አልቅነትና ሥልጣናትን ገፎ በአባቱ ቀኝ አለ ሁሉን አሸንፎ የሁሉ የበላይ ሆኖ የሚገዛው እኔ የማመልከው የጌቶች ጌታ ነው ኢየሱስ የጌቶች ጌታ ነው (4x) አምልኮ (3x) ይለኛል ዛሬ ደግሞ መንፈስህ በእጥፍ አግኝቶኛል በል ዘምር (3x) ይለኛል የሚወደኝ ጌታ ምህረት አድርጐልኛል ጠላት በዙሪያዬ መርዶ ሲያረዳኝ የጌታዬ ሰላም ከላይ ሲያገኘኝ አስባለኝ ተባረክ ጌታዬ ተባረክ ተባረክ ኢየሱስ ተባረክ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection