ምክርህ ሲሰራ አይቼ ተደስቻለሁ ማይከለከል ሃሳብህ አውቄዋለሁ ድንቅህን አይቼ ብገረም ቆምኩኝ ላመልክህ በሰው ሁሉ ፊት ተገልጧል አደራረግህ አዝ፦ ተባረክ ከዚህ ሌላ ምን እላለሁ ጌታዬ አንተ ነህ አውቄያለሁ ዘመኔን ከአንተ ጋር እንድኖር ጌታ በቃልህ/በምክርህ ደገፍከኝ እንዳልረታ (2x) አንተን አምኜ ወደፊት እራመዳለሁ ወሬ ሰምቼ ኋላዬን መቼ አያለሁ ዘለዓለሜ በእጅህ ነው ልቤ እንዳይሰጋ የምታመንህ ጌታዬ አለህ ከእኔ ጋር አዝ፦ ተባረክ ከዚህ ሌላ ምን እላለሁ ጌታዬ አንተ ነህ አውቄያለሁ ዘመኔን ከአንተ ጋር እንድኖር ጌታ በቃልህ/በምክርህ ደገፍከኝ እንዳልረታ (2x) የሰው ዓይን የለህ እንደሰው መቼ ታያለህ ጆሮህስ እንደሰማቸው መች ትፈርዳለህ መንገዱ ይሄ ነው ብሎ ሚመራህ የለም በምክርህ ግሩም ትክክል ጻድቅ አምላክ ነህ አዝ፦ ተባረክ ከዚህ ሌላ ምን እላለሁ ጌታዬ አንተ ነህ አውቄያለሁ ዘመኔን ከአንተ ጋር እንድኖር ጌታ በቃልህ/በምክርህ ደገፍከኝ እንዳልረታ (2x) ለዘሪ ዘርን የምትሰጥ ፍሬ እንዲበላ ከሕይወት እንዳይጐድል ሞቶ የኋላ ኋላ ለእኔም ቃልህን ሰጥተኸኛል ምን አስባለሁ ተስፋ ቢስ ሆኜ አልቀረሁም አከብርሃለሁ አዝ፦ ተባረክ ከዚህ ሌላ ምን እላለሁ ጌታዬ አንተ ነህ አውቄያለሁ ዘመኔን ከአንተ ጋር እንድኖር ጌታ በቃልህ/በምክርህ ደገፍከኝ እንዳልረታ (2x)