Song Lyrics

ከማስበውና

Kefa Mideksa
Hulu Beju New
ያለእርሱ ፈቃድ የበላ ተድላን የቀመሰ ማነው እስትንፋስ ያለው በሙሉ ሲመካ ሚያምረው በእርሱ ነው ለሃጥን ለጻድቁ ሰው ፀሐይን እኩል ያወጣል በግሌ ተገርሜርያለሁ ጌታ ከአይምሮዬ ያልፋል አዝ፦ ከማስበውና ከምገምተው በላይ ያደረገው እግዚአብሔር ነው (2x) የለመንኩትን ብቻ አይደለም ጨምሮ ሌላም ሰጥቶኛል ያልጠበኩትን በረከት ፀጋውን ደርቦልኛል ከእጆቹ የተቀበልኩት ስጦታው እንዴት መልካም ነው ቅሬታ የለም በልቤ ያረገው ሁሉ መልካም ነው አዝ፦ ከማስበውና ከምገምተው (በላይ) በላይ ያደረገው እግዚአብሔር ነው (2x) የምህረት ደጁ አልተዘጋም አምላኬ በዚህ አይታማም እርሱ እኮ ባለፀጋ ነው ለሚፈልጉት ቅርብ ነው (2x) አዝ፦ ከማስበውና ከምገምተው (በላይ) በላይ ያደረገው እግዚአብሔር ነው (2x) ያለእርሱ ፈቃድ የበላ ተድላን የቀመሰ ማነው እስትንፋስ ያለው በሙሉ ሲመካ ሚያምረው በእርሱ ነው ለሃጥን ለጻድቁ ሰው ፀሐይን እኩል ያወጣል በግሌ ተገርሜርያለሁ ጌታ ከአይምሮዬ ያልፋል አዝ፦ ከማስበውና ከምገምተው (በላይ) በላይ ያደረገው እግዚአብሔር ነው (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection