Song Lyrics

ስላሰብከኝ

Kefa Mideksa
Hulu Beju New
እንደነጋልኝ አይቶ ጠላቴ ከበሮውን ጥሎ ሮጠ ከፊቴ ድሌን ለማየት አልቻለምና ተራመድኩበት ነጋልኝና (2x) አዝ፦ የእኔ ጌታ በአንድ ቀን ጀንበር ታሪኬን ቀየርከው የእኔ ጌታ ሁሉን ውብ አድርገህ አንተ ነህ የሰራኸው ስላሰብከኝ ስለወደደከኝ ነው በቤትህ የቆምኩት ነግቶልኝ ነው በጉባኤ መሃል ለአንተ የዘመርኩት (2x) ሚታመኑህን የምታኮራ ያልተጠበቀን ድንቅ የምትሰራ አይቼሃለሁ ስትታደገኝ ከጠላቴ ቀስት ስታስመልጠኝ (2x) አዝ፦ የእኔ ጌታ በአንድ ቀን ጀንበር ታሪኬን ቀየርከው የእኔ ጌታ ሁሉን ውብ አድርገህ አንተ ነህ የሰራኸው ስላሰብከኝ ስለወደደከኝ ነው በቤትህ የቆምኩት ነግቶልኝ ነው በጉባኤ መሃል ለአንተ የዘመርኩት (2x) በጠዋት ማታ ጠብቀኸኛል ከጐኔ አለህ ምን ያሰጋኛል ጽኑ ግንቤ ነህ በጠላቴ ፊት ከአንተ ጋር ሆኜ አላውቅም ሽንፈት (2x) አዝ፦ የእኔ ጌታ በአንድ ቀን ጀንበር ታሪኬን ቀየርከው የእኔ ጌታ ሁሉን ውብ አድርገህ አንተ ነህ የሰራኸው ስላሰብከኝ ስለወደደከኝ ነው በቤትህ የቆምኩት ነግቶልኝ ነው በጉባኤ መሃል ለአንተ የዘመርኩት (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection