Song Lyrics

በቃ ብሎ

Kefa Mideksa
Hulu Beju New
አዝ፦ ብሩህ ቀን ሆኖልኛል ደስ ብሎኛል ጌታ ኢየሱስ ከፊቴ ወጥቶልኛል (2x) ነጋ ጠባ ተመስገን እለዋለሁ የሞት ደጃፍ ተዘግቶ አይቻለሁ (2x) መገረም ሞልቶኛል ጌታ መውደዱ ገኖ ሲወጣ ቆሜ ከመዘመር በቀር ምለውን አንዳች እስካጣ የክብሩ ጸዳል ሲያበራ እኔን ወደ እርሱ ሲጣራ ከልካይ አልነበረም ፊቱ ሲበራ ለእኔ መብራቱ አዝ፦ ብሩህ ቀን ሆኖልኛል ደስ ብሎኛል ጌታ ኢየሱስ ከፊቴ ወጥቶልኛል (2x) ነጋ ጠባ ተመስገን እለዋለሁ (እለዋለሁ) የሞት ደጃፍ ተዘግቶ አይቻለሁ (በዓይኔ) (2x) ዓይነጋም ብሎ ንጋቴን ሲረግምብኝ ሰማሁና እኔም ጠላት ያለውን ለአምላኬ ተናገርኩና ቀን አለው አምላኬ ከላይ በዓይኖቹ ወደ እኔ ሲያይ ጠላት መግቢያውን አጣ ዓይኔ አያየው ተቀጣ አዝ፦ ብሩህ ቀን ሆኖልኛል ደስ ብሎኛል ጌታ ኢየሱስ ከፊቴ ወጥቶልኛል (2x) ነጋ ጠባ ተመስገን እለዋለሁ (እለዋለሁ) የሞት ደጃፍ ተዘግቶ አይቻለሁ (በዓይኔ) (2x) በቃ ብሎ ገስጾ ወጀቡን ለእኔ አዞ አሳለፈኝ ጌታዬ ላክብረው በዜማዬ (2x) ላክብረው በዜማዬ (4x) ላክብረው በተራዬ (4x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection