Song Lyrics

ቅዱስ እግዚአብሔር ነው

Kefa Mideksa
Hulu Beju New
ቅዱስ እግዚአብሔር ያለ የነበርከው አንተ እኮ ነህ ለእኔ ከለላ የሆንከው (4x) ሌላማ ምን እከፍልሃለሁ ምሥጋና በፊትህ እሰዋለሁ (2x) አንተ እኮ ነህ በሕይወት እንድኖር ያደረከኝ ከዚያ ከጨለማ ከሞት የታደከኝ ስለ እኔ የቆሰልከው የደቀቀከው ጌታ በልቤ ይኖራል የአንተ ውለታ (2x) ይገርመኛል ከሞት መትረፌ ይገርመኛል በአንተ መታቀፌ ይገርመኛል ቸሩ የእኔ ጌታ ይገርመኛል ሆንክልኝ መከታ (3x) በረሃብ ዘመን ጥጋብ ሲሆንልኝ ያዩ ዛሬ ከእኔ ጋራ አንተን ያመልካሉ እኔም በመደነቅ በመገረም ሆኜ አመልክሃለሁኝ በመቅደስህ ቆሜ (2x) ይገርመኛል ከሞት መትረፌ ይገርመኛል በአንተ መታቀፌ ይገርመኛል ቸሩ የእኔ ጌታ ይገርመኛል ሆንክልኝ መከታ (3x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection