Song Lyrics

በእርሱ ነው

Kasahun Lema
Egziabher Ken Alew
አዝ፦ ሁሉን ያዘጋጀው እግዚአብሔር ነው የለም አንዳች ከኔ ብዬ ምለው በእርሱ ነው በእርሱ ነው በእርሱ ነው ሁሉ የሆነው በእርሱ ነው በእርሱ ነው በእርሱ ነው ሁሉ የሆነው (2x) ጽድቅ ነው ለኔስ ጌታዬ ጽድቅ ሆኖ የተቆጠረልኝ ጠላቴን ድባቅ የመታው ከእግሬ ስር ፈጥኖ የጣለልኝ ላክብረው ሥሙን በዜማ ቅኔዬን አሰካክቼ አልችልም ዝም ለማለት ልባርከው እጄን አንስቼ አዝ፦ ሁሉን ያዘጋጀው እግዚአብሔር ነው የለም አንዳች ከኔ ብዬ ምለው በእርሱ ነው በእርሱ ነው በእርሱ ነው ሁሉ የሆነው በእርሱ ነው በእርሱ ነው በእርሱ ነው ሁሉ የሆነው (2x) ተዓምርን ሰርቶ ያዳነኝ ሞቴንም በሞት የሻረው ትንሳዔን ለኔ ያወጀ ታሪኬን የለዋወጠው ምስኪኑን ከትቢያ አንስቶ በድል ላይ ድል የሚሰጠው እንዲህ ነው የታመንኩበት አምላኬ ብዬ የምለው አዝ፦ ሁሉን ያዘጋጀው እግዚአብሔር ነው የለም አንዳች ከኔ ብዬ ምለው በእርሱ ነው በእርሱ ነው በእርሱ ነው ሁሉ የሆነው በእርሱ ነው በእርሱ ነው በእርሱ ነው ሁሉ የሆነው (2x) የእግዚአብሔር ምህረቱ ገንኖልኝ በላዬ ጨለማዬም በራ ቆምኩኝ ቀና ብዬ (2x) ተከፋፈተልኝ የሰማዩም ደጃፍ አምላኬ ሲረዳኝ አየሁ አዲስ ምዕራፍ (4x) አዝ፦ ሁሉን ያዘጋጀው እግዚአብሔር ነው የለም አንዳች ከኔ ብዬ ምለው በእርሱ ነው በእርሱ ነው በእርሱ ነው ሁሉ የሆነው በእርሱ ነው በእርሱ ነው በእርሱ ነው ሁሉ የሆነው (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection