አዝ፦ ምድረበዳው ተዐምር መስሪያ ነው ባዶ ነገር ሙላትን ያያል ሰው አለቀ አበቃ ሲል የአንተ ተዐምር ይጀምራል አየሁ በዐይኔ የአንተን በጐነት በቀን በሌት ክንድህ ሲረዳኝ በማዕበሉ በወጀቡ ላይ ከፊት ቀድመህ በድል ስትመራኝ (2x) አይቼሃለሁ ከወዳጅ ይልቅ ወዳጅ የሆንከኝ አይቼሃለሁ አንተ ብቻ ነህ ክብር ያሳየኸኝ አይቼሃለሁ ይሆናል ያልክልኝ ሆኗል በሕይወቴ አይቼሃለሁ ድካሜን ሽረህ ሆንከኝ ጉልበቴ ያሰበውን ያቀደውን በሕይወቴ ፈጸመና ድንቅን ሰርቶ አስደነቀኝ የእኔ ጌታ እንደገና አዲስ ታሪክ አዲስ ምዕራፍ ጽፎ ሰጠኝ ከሰማይ እርሱ ካለ ሆነ እኮ ነው የለበት አዝዥ ከልካይ በአንተ መታመኔ አዋጣኝ ጌታዬ አላፈርኩብህም ያዋጣኛል ብዬ ጠላቴም ወዳጄ ግርም እስከሚለው ይሄው ተዐምርህን በዘመኔ አየሁ (2x) አዝ፦ ምድረበዳው ተዐምር መስሪያ ነው ባዶ ነገር ሙላትን ያያል ሰው አለቀ አበቃ ሲል የአንተ ተዐምር ይጀምራል አየሁ በዐይኔ የአንተን በጐነት በቀን በሌት ክንድህ ሲረዳኝ በማዕበሉ በወጀቡ ላይ ከፊት ቀድመህ በድል ስትመራኝ አይቼሃለሁ ከወዳጅ ይልቅ ወዳጅ የሆንከኝ አይቼሃለሁ አንተ ብቻ ነህ ክብር ያሳየኸኝ አይቼሃለሁ ይሆናል ያልክልኝ ሆኗል በሕይወቴ አይቼሃለሁ ድካሜን ሽረህ ሆንከኝ ጉልበቴ በአንተ እጅ ነው ሁሉ ነገር የሁሉ ቁልፍ የአንተ ብቻ ይሁን ያልከው ሲሆንልህ አይቻለሁ የለህ አቻ ሞተውን ያበቃውን ቃል አውጥተህ ትጥራለህ ተዘጋው ደጅ ገብተህ ሰላምህን ታውጃለህ በአንተ መታመኔ አዋጣኝ ጌታዬ አላፈርኩብህም ያዋጣኛል ብዬ ጠላቴም ወዳጄ ግርም እስከሚለው ይሄው ተዐምርህን በዘመኔ አየሁ (2x) አዝ፦ ምድረበዳው ተዐምር መስሪያ ነው ባዶ ነገር ሙላትን ያያል ሰው አለቀ አበቃ ሲል የአንተ ተዐምር ይጀምራል አየሁ በዐይኔ የአንተን በጐነት በቀን በሌት ክንድህ ሲረዳኝ በማዕበሉ በወጀቡ ላይ ከፊት ቀድመህ በድል ስትመራኝ አይቼሃለሁ ከወዳጅ ይልቅ ወዳጅ የሆንከኝ አይቼሃለሁ አንተ ብቻ ነህ ክብር ያሳየኸኝ አይቼሃለሁ ይሆናል ያልክልኝ ሆኗል በሕይወቴ አይቼሃለሁ ድካሜን ሽረህ ሆንከኝ ጉልበቴ