መንፈስህን ከእኔ አትውሰድብኝ (4x) ከአንተ ሌላ ሌላ ሌላ ወዳጅ የለኝ እንደ አንተ ሚሆንልኝ ከአንተ ሌላ ሌላ ሌላ ወዳጅ የለኝ እንደ አንተ ሚሆንልኝ የውስጡ ቆሽሾ ውጪውን አጥርቼ ትንኝ ያጠራው ግመል ያክል ውጬ ለሰው ታይታ ሚኖር ፈሪሳዊ ሆኜ ማለፍን አልሻም ከክብርህ ጐድዬ አቤቱ አምላኬ ሆይ በፊትህ ራሴን ላሳይ አግዘኝ እጠራሃለሁ ቸር አምላክ ነህ አውቅሃለው (2x) አትተወኝ አትጣለኝ ያላንተማ ሕይወት የለኝ (4x) እንደልቤ ሳይሆን ልሁን እንደልብህ ልወረስ በክብርህ እጄን ይያዝ እጅህ መንፈስህ መሪዬ ይሁን እረኛዬ በእቅፍህ ውስጥ ነው ክብሬም ዋስትናዬ አቤቱ አምላኬ ሆይ በፊትህ ራሴን ላሳይ አግዘኝ እጠራሃለሁ ቸር አምላክ ነህ አውቅሃለው (2x) መንፈስ ቅዱስ የሕይወቴ ትርጉም ነህ መንፈስ ቅዱስ የልቤ ማረፊያ መንፈስ ቅዱስ ሌላ አልመኝም መንፈስ ቅዱስ አጽናኝ ከአንተ ወዲያ አትተወኝ አትጣለኝ ያላንተማ ሕይወት የለኝ (4x)