አዝ፦ አቀላልቷል ሰማዩ ሊሰናበት ሌቱ ምን ጭጋጉ ቢያይል አይቀርም መንጋቱ ብርሃን ዘንበል ቢል ቢዳምን ደመና አዲስ ቀን ያሳያል ጌታ ቸር ነውና (2x) አሃሃ አንተን ታምኖ ማንስ ወድቆ ቀርቷል አሃሃ የታመነህ ሁሉን ጥሶ አልፏል አሃሃ መመኪያ ነህ ለምስኪኑ ጋሻ አሃሃ ማምለጫ ነህ ከጥፋት መሸሻ የእኔ አባት የእኔ ጌታ የእኔ ንጉሥ የእኔ አለኝታ በድካሜ ያልሳቅክብኝ እምባዬንም ያበስክልኝ ሳጸለቸኝ ተሸከምከኝ ከእናት ከአባት በላይ ሆንከኝ ኢየሱስ (3x) ከፍ በልልኝ (2x) አባት አለኝ እኔ ከአባትም አባት ያዋጣኛል ብዬ ያላፈርኩበት ያላፈርኩበት (2x) እግዚአብሔር ከአየልኝ ከቶ አንድም አይጐድልም አምላኬ ታማኝ ነው ሁኔታን አላይም እጠብቀዋለሁ በስፍራዬ ሆኜ ያለውን ያደርጋል ታማኝ ነው ጌታዬ እግዚአብሔር ያለው ይሆናል እግዚአብሔር ያለው ይጸናል እግዚአብሔር ያለው ይሳካል (2x) አዝ፦ አቀላልቷል ሰማዩ ሊሰናበት ሌቱ ምን ጭጋጉ ቢያይል አይቀርም መንጋቱ ብርሃን ዘንበል ቢል ቢዳምን ደመና አዲስ ቀን ያሳያል ጌታ ቸር ነውና (2x)