ኢየሱስ አለቴ ነህ ተደግፌሃለሁ አንተ ሁሉን ቻይ ነህ በጥላህ አርፋለሁ ከቶ አልጨነቅም ለነገዬ ብዬ ሁሉን የምትሆን ስላለህ ጌታዬ ሁሉን የምትሆን ስላለህ ጌታዬ (2x) አዝ፦ እልፍ ቃል ቢኖረኝ አንተን ማሞገሻ (2x) አመስግኜ አልጠግብም እስከመጨረሻ (2x) ባለ ብዙ ምህረት ባለ ብዙ ፀጋ ማንስ ወድቆ ቀርቷል አንተን የተጠጋ በጊዜው የምትደርስ ተቀድመህ አታውቅም ታማኝ ነህ አምላኬ እንደ ሰው አትዋሽም ታማኝ ነህ ኢየሱሴ እንደ ሰው አትዋሽም (2x) አዝ፦ እልፍ ቃል ቢኖረኝ አንተን ማሞገሻ (2x) አመስግኜ አልጠግብም እስከመጨረሻ (2x) ይገርመኛል ይደንቀኛል ጌታ ምህረትህ ለኔ ያለህ አላማ ፍፁም ደግነትህ (2x) ልትመለክ የሚገባህ ልትወደስ የሚገባህ (2x) ገናና ነህ የሁሉ የበላይ ከፍ በል በምድርም በሰማይ (2x) ብንሰግድልህ ብናመልክህ ስለሚገባህ ነው ክብር ይሁንልህ (2x) ክብር ይሁንልህ ክብር ይሁንልህ (8x)