Song Lyrics

ኢየሱስ የሕይወቴ

Kasahun Lema
Egziabher Ken Alew
በእቅፍህ መሃል ስፍራን ሰጠኸኝ ተደላድዬ እፎይ ብያለሁ አንተን አግኝቼ ክበር ጌታዬ እንዳልታወክ በቀኜ አለህ ውስጤ መች ሰግቶ ልቤም ይጣራል ኢየሱስ እያለ በፍቅርህ ነዶ (2x) አዝ፦ (ኢየሱስ) የሕይወቴ ትርጉም (ኢየሱስ) የሆንክልኝ ፍቺ (2x) (ኢየሱስ) ክብርን አይቻለሁ (ኢየሱስ) እኔስ በአንተ እጅ (2x) ሁሉን ቻይ አምላክ ወረት የማታውቅ እሩህሩህ ጌታ ፍቅርህ ማረከኝ የአንተ እንድሆን ልቤም ተረታ ሌላ አይገዛንም ከአንተ በስተቀር በምድር ያለው ሁሉ የሞላህ ባለ ፀጋ አምላክ አንተን ይዣለሁ (2x) ክበርልኝ (3x) አላየሁም ከአንተ የሚበልጥብኝ ንገስልኝ (3x) አልሰማሁም ከአንተ የሚበልጥብኝ አላየሁም ከአንተ የምበልጥብኝ አልሰማሁም ከአንተ የምበልጥብኝ (2x) ስትሾም ስትሸልም (አቤት ስታውቅበት) ደርሰህ ብርሃን (ስትሆን ቀን ለጨለመበት) ስታውቅበት ማበጃጀት ስታውቅበት መልክ መስጠት ስታውቅበት መሸላለም ማንም እንዳንተ የለም (2x) (ከተከስተ ጌትነት ጋር) አዝ፦ (ኢየሱስ) የሕይወቴ ትርጉም (ኢየሱስ) የሆንክልኝ ፍቺ (2x) (ኢየሱስ) ክብርን አይቻለሁ (ኢየሱስ) እኔስ በአንተ እጅ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection