አዝ፦ ህልሜ ሰምሯል በልጅነት ያየሁት በውሃ ውስጥ ያለፍኩለት በእሳት አልቀረሁም እንዳሰበው ያ ጠላቴ ሁሉን አለፍኩ አቅም ሆኖኝ ቸር አባቴ (2x) ሰምቼ ድላድ የነፃነት ፋና ከሞት አምልጫለሁ ከድቅድቅ ጨለማ የአዲስ ነገር ጅምር የታሪክ ምዕራፍ ጌታ ከፍቶልኛል የበረከት ደጃፍ አዝ፦ ህልሜ ሰምሯል በልጅነት ያየሁት በውሃ ውስጥ ያለፍኩለት በእሳት አልቀረሁም እንዳሰበው ያ ጠላቴ ሁሉን አለፍኩ አቅም ሆኖኝ ቸር አባቴ (2x) በእውነት የታመንክ ነህ ከቃልህ አንድ አይወድቅም ልትሰራ ተነስተህ አቅም አጥተህ አታውቅም የተረሳሁ ሲመስለኝ ስባል አስታዋሽ የለው አንተ ስትራራልኝ አዲስ ነገርን አየሁ ወደኋላ አልልም ያየልኝ አለና አምላኬ ከፊቴ ቀድሞኝ ወጥቷልና ልሂድ ልዘርጋ እንጂ ዱሩንም ልመንጥር አለ ካለሁበት የሚበልጥ ክብር (2x) አዝ፦ ህልሜ ሰምሯል በልጅነት ያየሁት በውሃ ውስጥ ያለፍኩለት በእሳት አልቀረሁም እንዳሰበው ያ ጠላቴ ሁሉን አለፍኩ አቅም ሆኖኝ ቸር አባቴ (2x)