Song Lyrics

ልነሳ ላመስግን

Kasahun Lema
Egziabher Ken Alew
በቃልህ ትእዛዝ በስልጣንህ በትር ሁሉን ትገዛለህ ላንተ ይሁን ክብር ከክብር ጋር ስፍራን በቀኝህ ሰጠኸኝ ምን ቢለፋ ቢጥር ጠላቴ አያገኘኝ አዝ፦ ልነሳ ላመስግን ዝቅ ዝቅ ብዬ ከእግርህ ስር ልሰዋ ምስጋና ክብር የሚገባህ ነህና (2x) ክብር የሚገባህ ነህና (4x) በሚታየው አልለውጥህም በሁኔታ አልገምትህም ቢመሽም ቢነጋም አውቃለሁ አንተን ለማመስገን እቆማለሁ 2x አዝ፦ ልነሳ ላመስግን ዝቅ ዝቅ ብዬ ከእግርህ ስር ልሰዋ ምስጋና ክብር የሚገባህ ነህና (2x) ክብር የሚገባህ ነህና (4x) ዘመኔን በክብርህ አስዋብከው ከአውሬና ከተኩላው አድነህ ከክብር ወደ ክብር መራኸኝ በእጅህ እጄን ይዘህ ታሪኬ ሆንክልኝ ትምክቴ ትርጉም ለሕይወቴ አመሰግናለሁ ከፍ በል ኢየሱስ መድኃኒቴ (2x) አዝ፦ ልነሳ ላመስግን ዝቅ ዝቅ ብዬ ከእግርህ ስር ልሰዋ ምስጋና ክብር የሚገባህ ነህና (2x) ክብር የሚገባህ ነህና (4x) እንደ ባለማዕረግ ተቀብለኸኛል እቅፍህ ይደላል ተመችተኸኛል የሕይወቴ እርካታ አንተ ከሆንክልኝ ዓይኔ ሌላ አያይም ምን ሊፈይድልኝ (2x) አዝ፦ ልነሳ ላመስግን ዝቅ ዝቅ ብዬ ከእግርህ ስር ልሰዋ ምስጋና ክብር የሚገባህ ነህና (2x) ክብር የሚገባህ ነህና (4x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection