Song Lyrics

አንተ ታማኝ ነህ

Kasahun Lema
Egziabher Ken Alew
ማለዳ ማለዳ ምህረትህ አዲስ ነው ታማኝነትህም እጅጉን ብዙ ነው (2x) ማለዳ ማለዳ ምህረትህ አዲስ ነው ታማኝነትህም እጅጉን ብዙ ነው (2x) አዝ፦ ታማኝ ነህ ታማኝ ታማኝ ነህ (4x) ጉልበት ሲዝል አቅም ጠፍቶ አይዞህ ባይ ሲታጣ ማን እንዳንተ የኔ ጌታ አለሁ ባይ መከታ ቢደገፉት እሚያኮራ ቢታመኑት ታማኝ አይገኝም ካንተ በቀር በምድርም በሰማይ አዝ፦ ታማኝ ነህ ታማኝ ታማኝ ነህ (4x) ጠላት ቢዋዥ በኃይልህ ላይ ትርፉ ድካሙ ነው ያልከው አይቀር ይፈጸማል ምክርህ የጸና ነው ትላንትናን እንደሰራህ ዛሬም ትሰራለህ ክንድህ አይዝል አስተማማኝ ሁልጊዜም ታማኝ ነህ አዝ፦ ታማኝ ነህ ታማኝ ታማኝ ነህ (4x) አንተን ይዞ ማን አፈረ ካንተ የተጠጋ አድነኸው አማረበት ከጠላት መንጋጋ ታሪክ መስራት ልማድህ ነው ክንድህ አይታክትም እርስትህን አሳልፈህ ለጠላት አትሰጥም አዝ፦ ታማኝ ነህ ታማኝ ታማኝ ነህ (4x) ማለዳ ማለዳ ምህረትህ አዲስ ነው ታማኝነትህም እጅጉን ብዙ ነው (2x) አዝ፦ ታማኝ ነህ ታማኝ ታማኝ ነህ (4x) በዙሪያዬ ጋሻ የእሳት ቅጥር ሆነ ከጥፋት ማምለጫ ኢየሱስ አለቴ ነህ በለመለመ መስክ መምራት ስታውቅበት የዘላለም ብርሃን ቀን ለጨለመበት የዘላለም ብርሃን ነህ የዘላለም ብርሃን (8x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection