ወይ የምታልፍ ብሎ ያለወትሮው ሞልቶ ዮርዳኖስ ቢፎክር ቢቆምም ከፊቴ በዳር አስከ ክብር እሄዳለሁ አልፈራም ጌታ ነው ጉልበቴ ረግጬው አልፋለሁ ጌታ ነው ጉልበቴ ኢየሱስ ነው ጉልበቴ አዝ፦ ቢጮህም አያሸንፍም ቢጎርፍም ከልኩ አያልፍም የጠራኝ ከኔ ጋራ ነው ለጠላት ዕድል አልሰጠው (2x) ለጠላት ዕድል አልሰጠው (4x) ሰባት እጥፍ ብያነድ ጠላቴ እሳቱን አብዝቶ ከከፍታዬ ላይ አልወርድም ስፍራ አለቅም ከቶ የመቆሜ ሚስጥር ጌታ እንጂ አይደለም ሁኔታ የታመንኩበትን አውቃለሁ አንደማይረታ (2x) አዝ፦ ቢጮህም አያሸንፍም ቢጎርፍም ከልኩ አያልፍም የጠራኝ ከኔ ጋራ ነው ለጠላት ዕድል አልሰጠው (2x) ለጠላት ዕድል አልሰጠው (4x) ጠላቴን ከፊቴ አውጥቶት አጥፋው ብሎ አዞኛል አስጨናቂውን ዘንግ ጌታ ፈጥኖ ሰብሮልኛል የከፍተኛነቴ ሰይፍ ብቃቴም እርሱ ነው አትፍራ ሰላለኝ አልፈራም ጌታ ከኔ ጋር ነው (2x) ጌታ ከኔ ጋር ነው(4x) አዝ፦ ቢጮህም አያሸንፍም ቢጎርፍም ከልኩ አያልፍም የጠራኝ ከኔ ጋራ ነው ለጠላት ዕድል አልሰጠው (2x) ለጠላት ዕድል አልሰጠው (4x) ከትላንቱ ይልቅ ዛሬ አስደንቆኛል (2x) እግዚአብሔር ስራዬን ሁሉ ሰርቶልናል (2x) ላመስግነው አንጂ ስሙን በዝማሬ (2x) ለጠላቴ ሃዘን የድል ቀን ነው ዛሬ የድል ቀን ነው ዛሬ (2x) አዝ፦ ቢጮህም አያሸንፍም ቢጎርፍም ከልኩ አያልፍም የጠራኝ ከኔ ጋራ ነው ለጠላት ዕድል አልሰጠው (2x) ለጠላት ዕድል አልሰጠው (9x)