Song Lyrics

የጸና ግንብ

Kasahun Lema
Akelaltoal Semawyu
የጸና ግንብ የሕይወቴ ምርኩዝ ሞገሴ ነው ለእኔ በእርሱ ብርታት በእርሱ ፀጋ እኮ ነው ጸንቼ መቆሜ ተዐምረኛ የተዐምራት አምላክ ድንቅን የሚሰራ ከጌታዬ ከኢየሱሴ በቀር የለም እውነተኛ ታሪክ ተገልብጦ ጠላቴም ተመቶ በቆፈረው ጉድጓድ እርሱ ራሱ ገብቶ ስላየሁ የጌታዬን ማዳን ለእርሱማ አምልኮ ያንስበታል ስላየሁ የኢየሱሴን ማዳን ለእርሱማ አምልኮ ያንስበታል ለእርሱማ አምልኮ ያንስበታል ለእርሱማ ምሥጋና ያንስበታል (2x) የተጣለ ፈጽሞ እንዳይጠፋ በምክሩ እያሰበ ማክበር ያውቃል በፀጋ ላይ ፀጋ እይደራረበ አይቻለሁ ይሄ በእኔ ሆኖ በሕይወት ዘመኔ እርሱ ብቻ ከአጠገቤ ቆሞ አለሁ ሲል ከጐኔ ታሪክ ተገልብጦ ጠላቴም ተመቶ በቆፈረው ጉድጓድ እርሱ ራሱ ገብቶ ስላየሁ የጌታዬን ማዳን ለእርሱማ አምልኮ ያንስበታል ስላየሁ የኢየሱሴን ማዳን ለእርሱማ አምልኮ ያንስበታል ለእርሱማ አምልኮ ያንስበታል ለእርሱማ ምሥጋና ያንስበታል (2x) የበላይ ቢሉህ ቢያሞጋግሱህ አንተን አይገልጹም ትልቅ ነህ ቢሉህ የበላይ ብልህ ባሞጋግስህ አንተን አልገልጽህ ትልቅ ነህ ብልህ ከሁሉ በላይ ነህና (4x) ከሁሉ በላይ ትልቅ ነህ ከሁሉ በላይ ገናና (2x) አይጓደል አምልኮዬ ለአንተ ለጌታዬ (2x) አይጓደል ምሥጋናዬ ለአንተ ለጌታዬ (2x) ከሁሉ በላይ ነህና (4x) ከሁሉ በላይ ትልቅ ነህ ከሁሉ በላይ ገናና (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection