Song Lyrics

ኢየሱስ

Kasahun Lema
Akelaltoal Semawyu
አይታለፍም ብዬ ደምድሜ ነበረ ጌታዬ በአንተ ሁሉ ተውቦ ሰመረ ምን ይሳንሃል ሁሉን ልጸራው ችለሃል ተራራውንም ደልዳላ ሜዳ አርገሃል (ኢየሱስ) ሕይወቴ ነህ አንተ (ኢየሱስ) ትርጉም ማንነቴ (ኢየሱስ) በቀኝህ ያኖርከኝ (ኢየሱስ) የልቤ ኩራቴ (ኢየሱስ) ምሥጋናዬ አንተ ነህ (ኢየሱስ) አንተን እጠራለሁ (ኢየሱስ) ስምህ ሲያለመልም (ኢየሱስ) እንደሚፈስ ዘይት ነው አምላክ ሆይ በአንተ የማያልፍ የለም ምርኩዜ አንተ ነህ ሸንበቆ አይደለህ ትላንት ያደረከው እምነት ሆኖኛል የማይጥል እጅህ እጄን ይዞኛል አልተረታሁም እኔስ በስምህ ተወረርጄ ፊቴ አላፈረም መልሴ ፈጠነ ገባልኝ ከእጄ የማይቻለው በአንተ ተችሎ አይቼዋለሁ ለስምህ ክብር ለጌትነትህ እዘምራለሁ አለኝ ወዳጅ የምለው አለኝ ውስጤ ሚወደው አለኝ ሚስጥረኛዬ ሳይንቅ ገብቷል ጓዳዬ አለኝ ወዳጅ የምለው አለኝ ውስጤ ሚወደው አለኝ ሚስጥረኛዬ ኢየሱስ ገብቷል ጓዳዬ ኢየሱስ ገብቷል ጓዳዬ (4x) እረኛዬ ነህ ከአንበሳው ከድብ አድነኸኛል አበቃ ሲባል የሁሉንም ቁልፍ ይዘህ ደርሰሃል ታዲያ ብዘምር ከሆንኩት በላይ መች ይበዛና ታሪኬ ሆነህ አዳፋ ልብሴን ጥለሃልና አለኝ ወዳጅ የምለው አለኝ ውስጤ ሚወደው አለኝ ሚስጥረኛዬ ሳይንቅ ገብቷል ጓዳዬ አለኝ ወዳጅ የምለው አለኝ ውስጤ ሚወደው አለኝ ሚስጥረኛዬ ኢየሱስ ገብቷል ጓዳዬ ኢየሱስ ገብቷል ጓዳዬ (4x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection