መታመኛዬ መታመኛዬ እግዚአብሔር በዙፋኑ አለ ሁሉንም አዲስ የሚያደርገው ቀን ቀጥሮ ድንገት ከተፍ የሚል ታሪክን በታሪክ ሚሽረው ጌታ ነው የሁሉ ቁልፍ ያለው ጌታ ነው እኔ ምታመነው ጌታ ነው ድንገት ከተፍ የሚል ጌታ ነው ሁሉ የሚቻለው ሳልሰጋ እኖራለሁ በአንተ ተማምኜ (2x) እጅግ በሚመቸው ትከሻ ላይ ሆኜ (2x) ተራሮች ቢወርዱ ወደባሕር ልብ (2x) የያዝኩት አንተን ነው የነፍሴ መልህቅ (2x) የዘለዓለም አምላክ የሕይወት መገኛ ጽኑ ግንብ ሆንክልኝ ለእኔ መታመኛ (2x) መታመኛ መመኪያዬ እኔ አለኝ የምለው ኢየሱስ ጌታዬ የእኔ ጋሻ ማምለጫዬ የዘለዓለም ክብሬ ሆነኝ አለኝታዬ መመኪያዬ ኢየሱስ ጌታዬ (4x) የድል መሰረቴ መደላደላዬ (2x) እንድኖር ያደረከኝ በአንተ እፎይ ብዬ (2x) ጀርባ አልሰጠኸኝም በጠላቴ ፊት በሚጠላኝ ጊት ይልቁን ቀባኸኝ ራሴን በዘይት (2x) ነፍሴን በከበረው ሰረገላ አስቀምጠህ ሞላኸኝ በምሥጋና የእኔ ጌታ እንደአንተማ ለእኔ ማንም የለም ሾሜሃለሁ ግዛ በሕይወቴ ለዘለዓለም ኢየሱሴ እንደ አንተማ ለእኒ ማንም የለም ሾሜሃለሁ ግዛ በሕይወቴ ለዘለዓለም መታመኛ መታመኛዬ ተባረክ ጌታዬ (4x) የታል የትናንቱ የከበደኝ ነገር (2x) እንደጉም በነነ ከላይ ስትናገር (2x) አዲስ የድል ምዕራፍ ተቀዳጅቻለሁ (2x) በአንተ በአምላኬ ቅጥሩን ዘልያለሁ (2x) የዘለዓለም አምላክ የሕይወት መገኛ ጽኑ ግንብ ሆንክልኝ ለእኔ መታመኛ (2x) መታመኛ መታመኛዬ ተባረክ ጌታዬ (4x)