ምነው ሰማያትን ቀደህ ብትወርድልኝ ብዬ እኔ ስጣራ ታየኛለህ (2x) ለካስ ታየኛለህ ከሰማያት በላይ ለእኔ የምትራራ ታየኛለህ (2x) ያልተጠባበኩት የክብርህን ስራ ገልጸህ ልታሳየኝ ታየኛለህ (2x) አሁን ተረዳሁት ሁሉ ለበጐ ነው የአንተ አላማ ገባኝ ታየኛለህ (2x) ታየኛለህ ስጠራህ ትሰማኛለህ ታየኛለህ የልቤን ታደምጠኛለህ ታየኛለህ የደምህ ኪዳን አለኝ ታየኛለህ ላትጥለኝ ስለያዝከኝ ኢየሱስ (2x) (ኢየሱሴ) አንተ ነህ ለእኔ ዋሴ (ለእኔ ዋሴ) ፍቅርህን አስባለሁ (ፍቅርህን አስባለሁ) ዘለዓለም እወድሃለሁ (ዘለዓለም ወድሃለሁ) (2x) አምንሃለሁ አትጥልም አንተ አትጐዳም አምንሃለሁ ጀርባ አትሰጥም ደርሰህ እንደባዳ አምንሃለሁ መጠጋት ማቀፍ ባሕሪህ አምንሃለሁ ተመካሁ በማይጥል ፍቅርህ (2x) ኢየሱስ (2x) (ኢየሱሴ) አንተ ነህ ለእኔ ዋሴ (ለእኔ ዋሴ) ፍቅርህን አስባለሁ (ፍቅርህን አስባለሁ) ዘለዓለም እወድሃለሁ (ዘለዓለም ወድሃለሁ) (2x) አምንሃለሁ ታማኝ ነህ ከምንም በላይ አምንሃለሁ ቃል ሳይሆን የልብን የምታይ አምንሃለሁ እንደሰው አይተህ አተፈርድም አምንሃለሁ መንገድ ላይ ጥለህ አትሄድም (2x) ምነው ሰማያትን ቀደህ ብትወርድልኝ ብዬ እኔ ስጣራ ታየኛለህ (2x) ለካስ ታየኛለህ ከሰማያት በላይ ለእኔ የምትራራ ታየኛለህ (2x) ያልተጠባበኩት የክብርህን ስራ ገልጸህ ልታሳየኝ ታየኛለህ (2x) አሁን ተረዳሁት ሁሉ ለበጐ ነው የአንተ አላማ ገባኝ ታየኛለህ (2x) ታየኛለህ ስጠራህ ትሰማኛለህ ታየኛለህ የልቤን ታደምጠኛለህ ታየኛለህ የደምህ ኪዳን አለኝ ታየኛለህ ላትጥለኝ ስለያዝከኝ