Song Lyrics

ይሄ ነው የእኔ ጌታ

Kasahun Lema
Akelaltoal Semawyu
አዝ፦ ይሄ ነው የእኔ ጌታ ታሪኬን የለወጠው መራራውን ያጣፈጠልኝ ሕይወቴን መልክ የሰጠው (2x) እኔስ ለዚህ ጌታ እኖርለታለሁ ከኖርኩለት በላይ እኖርለታለሁ እኔስ ለኢየሱሴ እኖርለታለሁ ከሆንኩለት በላይ እሆንለታለሁ ከልካዩ ከልክሎት ገድቦት ነው እንጂ ሲያስገመግም መጥቶ ማዐበሉ ከደጅ ነገር ተገልብጦ መርገሙ በባርኮት ለሞት የታጨው ሰው በዝቶለታል ሕይወት አዎ ልዘምርለት አዎ ልቀኝለት አዎ በእርሱ አይደለም ወይ እኔ ሰው የሆንኩት ገና ስለእርሱ ክብር ገና ስለእርሱ ዝና ገና እኔ ዘምሬ ገና መች ጠገብኩና ገና ከሆንኩት በላይ ገና ብሆን ሲያንስ ነው ገና ያደረገልኝን ገና እኔ ነኝ የማውቀው በእሳት ውስጥ አለፌያለሁ አላቃጠለኝም በውኃም አልፌያለሁ አላሰጠመኝም ምህረቱ እንደጋሻ እየከለለኝ የትላንትና ሃዘኔ ጌታ አስረሳኝ ምን ልበል ምን ልናገር ተመስገን ከማለት በቀር እርሱ ነው ሰው ያደረገኝ ትላንትን እያሻገረኝ ቀን አለህ ስለው ቀን ሰጠኝ ከቀን በላይ ቀን አሳየኝ ቀን በቀን ምህረቱ በዝቶ አቆመኝ ቅኔውን ሞልቶ አዝ፦ ይሄ ነው የእኔ ጌታ ታሪኬን የለወጠው መራራውን ያጣፈጠልኝ ሕይወቴን መልክ የሰጠው (2x) እኔስ ለዚህ ጌታ እኖርለታለሁ ከሆንኩለት በላይ እሆንለታለሁ እኔስ ለኢየሱሴ እኖርለታለሁ ከሆንኩለት በላይ እሆንለታለሁ ደመናም ሳይታይ ንፋስም ሳይኖር ሁሉን ከላይ አዞ የሚያሰማምር ጌታ አይደለም ወይ ሁሌም ሁሉን ቻይ በስራው ትክክል የሌለው ከልካይ አዎ ልዘምርለት አዎ ልቀኝለት አዎ በእርሱ አይደለም ወይ እኔ ሰው የሆንኩት ገና ስለእርሱ ክብር ገና ስለእርሱ ዝና ገና እኔ ዘምሬ ገና መች ጠገብኩና ገና ከሆንኩት በላይ ገና ብሆን ሲያንስ ነው ገና ያደረገልኝን ገና እኔ ነኝ የማውቀው ትሞትብኛለህ አልልም ሕያው ነህ ትቀርብኛለህ አልልም ቅርቤ ነህ ትከዳኛለህ ነህ አልልም ታማኝ ነህ አምላኬ ከምንም ከማንም ልዩ ነህ ልዩ ነህ የእኔ ጌታ ለእኔ ልዩ ነህ ልዩ ነህ የእኔ ወዳጅ ለእኔ ልዩ ነህ ልዩ ነህ የእኔ ጌታ ለእኔ ልዩ ነህ (አንተ ልዩ) ልዩ ነህ ኢየሱሴ ለእኔ ልዩ ነህ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection