Song Lyrics

አድነነ

Kasahun Lema
Akelaltoal Semawyu
የእውነት መልክ ያለው ከእውነት የተጣላ የጊዜውን ያየ የነገው ተላላ በሌላው ላይ ፈራጅ ጣቶቹን ቀሳሪ ስለእራሱ ኑሮ ሕያውን ቀባሪ ካባው የሸፈነው መቃብርነቱን የምላሱ ቂቤ አጥምዶ አረካለት የልብ አውሬነቱን አዝ፦ አድነነ ከመዐቱ ሰውረን ስማን አምላክን ወመድሃኒን (2x) (ይቅርብኝ) ላይጠቅመኝ ይቅርብኝ (ይቅርብኝ) ቢቀርብኝ ሞት ነው (ይቅርብኝ) ለካ የተወዳጀኝ (ይቅርብኝ) ተንቀሳቃሽ ሞት ነው (ይቅርብኝ) የፍቅር ሰው መሳይ (ይቅርብኝ) የወንድም አታላይ (ይቅርብኝ) ስንቱን ወጥቶ ጣለው (ይቅርብኝ) ያልብሾት ተናኝ ታረቅ ከእራስህ ጋር ወገኔ ሁሉ ያመልጥሃል ስትል ለእኔ መኖር ልመድ እንጂ ለሌላዉ ያ ነው የሕይወት ተድላ ደስታዉ (2x) አዝ፦ አድነነ ከመዐቱ ሰውረን ስማን አምላክን ወመድሃኒን (2x) ጣኦት ተሰይፎ መቅደሽን ይዘርፋል ህሊናህን ጥሶት አካልህ ይሮጣል ልጓም አበጂለት ራስህ ከአንተ ወጥቷል ሁለት ሰው ሆነህ መታወቂያህ ጠፍቷል ሩቅ አሳቢ ሆነህ በቅርቡ አዳሪ የአፍ ብቻ አርበኛ አስጐምጅቶ በላ አንቱ ፈሪሳዊ እኔነቴን በእኔው ያለ የእኔው ጠላቴ አላወጣው ውስጤ በእኔው ነዋሪ ቤቴ ኖሮ እንዳያጠፋኝ ንቃልኝ ውስጠቴን (2x) ማረን ማረን ይቅር በለን ስማን ስማን ተቀበለን (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection