እግዚአብሔር በድንቅ የረዳው (ኧረ እንደ እኔስ ማነው) (3x) ሞቷል ሲባል ሕይወት ያየ ሰዉ (ኧረ እንደ እኔስ ማነው) (3x) የጠላቱን ውድቀት ያየ ሰዉ (ኧረ እንደ እኔስ ማነው) (3x) ጌታ ከላይ ተሻገር ያለዉ (ኧረ እንደ እኔስ ማነው) (3x) እግዚአብሔር ትልቅ ነው ቢኮሩበት ያኮራል ስሙ ከስም በላይ ነው ሲጠሩት ያስመልጣል ኮራ ብዪ እኖራለሁ ያመንኩትን አውቃለሁ ሹመቴ ሽልማቴ ከፍታዬ ኢየሱስ ነው አዝ፦ ከፍታዬ ነው ጌታ ከፍታዬ (4x) ምሥጋና አለኝ ልቤ ተነሳ (እንደገና) (3x) በእርሱ ያለፍኩትን ያን ቀን አሰበና (እንደገና) (2x) አምልኮ አለኝ ልቤ ተነሳ (እንደገና) (3x) እርሱ ያደረገልኝን ዉለታ አሰበና (እንደገና) (2x) ገና አለኝ እኔስ ገና ለአንተ ብዙ ምሥጋና ዉለታህ አለብኝና (2x) ዉለታ አለብኝና (8x) ያየሁትን ሳላይ አልቀርም መንገድ ላይ እደርሳለሁ ከግቤ ህልም አለኝ ከሰማይ ሰው አይደለምና የተናገረኝ የጠራኝ ታማኝ ነው ቃሉን የሰጠኝ ዮሴፍ በሕይወት አለ ያውም በክብር ራዕዩን የሰጠ አለና እግዚአብሔር ሰረገላው ከደጅ ቆሟል ለማስረጃ ይሄው ዘመን መጣ ወደክብር መውጫ አዝ፦ ከፍታዬ ነው ጌታ ከፍታዬ (4x) ዓለም ሳይፈጠር በልጁ ወዶኛል ልክደው የማልችለው ይህ እውነት ገብቶኛል የብረቱ መዝጊያ ምን ቢቆም ከፊቴ አውቆ ይከፈታል ጌታ አለ ከፊቴ ንጉሥ የወርቁን ዘንግ ዘረጋልኝና ያለህግ አስገባኝ ከፋፈተውና ገና ሳልናገር ሁሉ ተሰካካ የታመንኩት አምላክ ቀድሞ ወጥቷል ለካ አዝ፦ ከፍታዬ ነው ጌታ ከፍታዬ (4x)