Song Lyrics

ዝርግፍ ጌጤ

Kasahun Lema
Akelaltoal Semawyu
አዝ፦ ዝርግፍ ጌጤ ነህ ኩራቴ ኢየሱሴ ማዕረጌ ሁሉ በአንተ ሆነ በአምላኬ ሁሉ በአንተ ሆነ በአምላኬ (4x) እንደዐይኖችህ ብሌን ተጠንቅቀህልኝ የከበደ ሸክሜን ከእኔ አራግፈህልኝ ቀና ብዬ እንድኖር አንተ አድርገኸኛል ከክብር ጋር ስፍራን ጌታ ሰጥተኸኛል የእኔ አባት የእኔ ጌታ መመኪያዬ ነህ ጌታዬ የእኔ አባት የእኔ ጌታ ማረፊያዬ ነህ ጌታዬ አዝ፦ ዝርግፍ ጌጤ ነህ ኩራቴ ኢየሱሴ ማዕረጌ ሁሉ በአንተ ሆነ በአምላኬ ሁሉ በአንተ ሆነ በአምላኬ (4x) እኔ ያላየሁትን አንተ አይተህልኝ የሕይወቴን ጐዳና ያቀናናህልኝ ከእኔ በላይ ለእኔ አንተ ታስባለህ አላማህ መልካም ነው በእኔ ላይ ያለህ የእኔ አባት የእኔ ጌታ መመኪያዬ ነህ ጌታዬ የእኔ አባት የእኔ ጌታ ማረፊያዬ ነህ ጌታዬ አዝ፦ ዝርግፍ ጌጤ ነህ ኩራቴ ኢየሱሴ ማዕረጌ ሁሉ በአንተ ሆነ በአምላኬ ሁሉ በአንተ ሆነ በአምላኬ (4x) ያሰብከው ሆነልኝ አንተ ለእኔ ያልከው አንተ ይሁን ስትል ጌታ ከልካይ ነው ያሰብከው ይሆናል ያየኸው ይጸናል እንደ ቃልህ ሆነህ ታምነህ ተገኝተሃል የእኔ አባት የእኔ ጌታ መመኪያዬ ነህ ጌታዬ የእኔ አባት የእኔ ጌታ ማረፊያዬ ነህ ጌታዬ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection