Song Lyrics

አላገኘሁም ፈልጌ

Kalkidan (Lili) Tilahun
Yitayegnal Bizu Neger
አላገኘሁም ፈልጌ ፈልጌ ለአንተ የምሰጠውን መስዋት አድርጌ (2x) እራሴን ሰውነቴን መሰዊያው ላይ ላኑርልህ አሃሃ ቅድስና ደስ የሚያሰኝ ሕያው መስዋት ይሁንልህ ይሁንልህ (2x) አላገኘሁም ፈልጌ ፈልጌ ለአንተ የምሰጠውን መስዋት አድርጌ (2x) ከፍ ያለው በዙፋኑ ላይ ተከብሮ ያለ በሠማይ ምሥጋና አይነስበት ክብርም ይጨመርለት አምልኮ አይነስበት ክብርም ይጨመርለት ዝማሬም አይነስበት ክብርም ይጨመርለት የማይመረመረው ድንቅ ነገር የማይቆጠረው ተዓምራት (2x) ሁሉን ያደረገው ማነው እግዚአብሔር ነው (2x) ይህ የሰራ ማነው እግዚአብሔር ነው አሃ (2x) ክብር ሁሉ ለእርሱ ይሁን (4x) አላገኘሁም ፈልጌ ፈልጌ ለአንተ የምሰጠውን መስዋት አድርጌ (2x) እራሴን ሰውነቴን መሰዊያው ላይ ላኑርልህ አሃሃ ቅድስና ደስ የሚያሰኝ ሕያው መስዋት ይሁንልህ ይሁንልህ ኃይል የሌለውን ምንኛ ረዳኸው ጥበብ ያጣውን ምንኛ መከርከው የደከመውን ምንኛ አገዝከው የተጣለውን ምንኛ አነሳኸው (2x) ረድኤቴ አንተ አይደለህም ዎይ (4x) የረዳኝ የረዳኝ ጌታዬ ባለውለታዬ ባለውለታዬ ባለውለታዬ (2x) ሕይወቴን የሞላህልኝ ኢየሱስ ተመስገንልኝ ጉልበቴን ያጸናህልኝ ኢየሱስ ተመስገንልኝ መንገዴን ያቀናህልኝ ኢየሱስ ተመስገንልኝ ጽዋዬን የሞላህልኝ ኢየሱስ ተመስገንልኝ አንተ እጅህን ትከፍታለህ አሃ ትከፍታለህ ኦሆ ትከፍታለህ ሕይወት ላለው ሁሉ መልካም ነገር ታጠግባለህ ኦሆ ታጠግባለህ አሃ (2x) እንደገና አፌን ሳቅ ሞላው ዓይኔም አየችው ጌታ ይሄ ነው እንደገና እንደገና አፌን ሳቅ ሞላው ዓይኔም አየችው ጌታ ይሄ ነው (3x) አምላኬ ይሄ ነው ጌታ ይሄ ነው ህልም ነው ወይ እውን እንዴት ይገርማል እግዚአብሔር ሲሰራ አንድ ቃል ያበቃል (2x) ከፍ ያለው በዙፋኑ ላይ ተከብሮ ያለ በሠማይ ምሥጋና አይነስበት ክብርም ይጨመርለት አምልኮ አይነስበት ክብርም ይጨመርለት ዝማሬም አይነስበት ክብርም ይጨመርለት ምሥጋና አይነስበት ክብርም ይጨመርለት አምልኮ አይነስበት ክብርም ይጨመርለት ዝማሬም አይነስበት ክብርም ይጨመርለት
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection