ሌላ ነገር አይደለም ነፍሴን የሚያረካት አምላክ ሆይ አንተ ናና በመገኘትህ አርካት ሌላ ነገር አይደለም ነፍሴን የሚያረካት አምላክ ሆይ አንተ ናና በመገኘትህ አርካት (5x) አንዳንዶች ገንዘብ ይላሉ አንዳንዶች ዝና ይላሉ አንዳንዶች ዘመድ ይላሉ አንዳንዶች ዕውቀት ይላሉ እኔ ግን እርግጠኛ ነኝ አንተው ነህ የምትበልጠው (2x) እግዚአብሔር ሆይ አንተ ብቻ ነህ ለሰዎች ሁሉ መፍትሄ ያለህ ጌታ ኢየሱስ ሆይ አንተ ብቻ ነህ ለሰዎች ሁሉ መፍትሄ ያለህ ነፍሴ ወደደችህ ወዴት ትገኛለህ ስፍራውን አሳየኝ የት ታሰማራለህ (2x) ብርና ወርቅ አያጓጓኝም ልቤን አይነካኝም ዓይኔን አይስበኝም የሚያጓጓኝ የእግዚአብሔር መንግሥት ነው ርሃቤ ጥማቴ ጽድቁ ነው ጽድቁ ነው (2x) አንተን ነው ነፍሴ የተጠማችው አንተን ነው ነፍሴ የተመኘችው የአንተን ስጦታ መፈለግ ትታለች አንተን እራህን ትፈልጋለች የአንተን በረከት መፈለግ ትታለች አንተን ራስህን ትፈልግሃለች ምን አዲስ ነገር አለ ከዚህ ፀሐይ በታች የእግዚአብሔር ልጅ ነው እንጂ ለሰዎች የሚበጅ (2x) ጌታ ኢየሱስ ነው እንጂ ለሰዎች የሚበጅ ነፍሴ ወደደችህ ወዴት ትገኛለህ ስፍራውን አሳየኝ የት ታሰማራለህ (2x) መዝገቤ እኮ አንተ ጋር ነው መዝገቤ በሰማይ መዝገቤ በአለበት ልቤስ በዚያ አይደል ወይ (3x) ነፍሴ ወደደችህ ወዴት ትገኛለህ ስፍራውን አሳየኝ የት ታሰማራለህ (2x) እግዚአብሔር ሆይ አንተ ብቻ ነህ ለሰዎች ሁሉ መፍትሄ ያለህ ጌታ ኢየሱስ ሆይ አንተ ብቻ ነህ ለሰዎች ሁሉ መፍትሄ ያለህ