Song Lyrics

አለኝ የምለው

የኔ መመኪያ የኔ ክብር እግዚአብሔር ነው 4* አለኝ የምለው ተስፋ ማረገው የምመካበት ፊትህን ብቻ ነው ፊትህን ወደኔ ከመለስክልኝ በኔ ደስ ካለህ ካልተቆጣኸኝ አይኖችህ ካዩኝ ጆሮህ ከሰማኝ ይሄ ይበቃኛል እረካለሁኝ አለኝ የምለው ተስፋ ማረገው የምመካበት ፊትህን ብቻ ነው ደስ የሚያሰኝህን አይ ዘንድ እወዳለሁ አንተን ደስ እንዲልህ ሁልግዜ እተጋለሁ እኔ ደስ የሚለኝ ሀሳቤ ሚሞላው አንተ በኑሮዬ ስትረካ ብቻ ነው ከአእላፋት ወርቅና ብር ይልቅ ጌታ ፊትህ ይሻለኛል 2* ከአእላፋት ወርቅና ብር ይልቅ ትዛዛት ይሻሉኛል 2* የኔ መመኪያ የኔ ክብር ኦሆሆ እግዚአብሔር ነው የኔ መመኪያ አለኝ የምለው እግዚአብሔር ነው አለኝ የምለው ተስፋ ማረገው የምመካበት ፊትህን ብቻ ነው
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection