Song Lyrics

ማነው

እስትንፋስ ያላቸው ፍጥረታት በሙሉ እግዚአብሔር ትልቅ ነው ትልቅ ነው ይላሉ አንዳንዱ ፈልጎ አንዳንዱ በግድ አያስደንቅም ወይ ለ እግዚአብሔር ሲሰግድ ማነው እንዳንተ ማነው ማነው እንዳንተ ማነው አህዛብ ደንግጡ ምድርም ትፍራው ፈላጩ ቆራጩ እሱ ብቻ ነው ታፍሮና ተከብሮ በዙፋኑ ያለው ከእግዚአብሔር በስተቀር የትኛው አምላክ ነው ማነው እንዳንተ ማነው ማነው እንዳንተ ማነው የእድሜ ባለፀጋ ሁሌ አንፀባራቂ ለሰማይ ለምድሩ ለፍጥረቱ በቂ ከዘላለም በፊት ከጥንት የነበረው እግዘብሔርን በድሜ የሚበልጠው ማነው ማነው እንዳንተ ማነው ማነው እንዳንተ ማነው የነገስታትን ወገብ የሚፈታ የኔ ጌታ ኦሆሆ የኔጌታ ብቻውን ብዙ ገጥሞ የሚረታ የኔጌታ የኔ ጌታ ቃላቶች ተጨምቀው አንድ ቃል ቢሆኑ ያንተን ትልቅነት ሊገልጹት አይችሉም ማነው የላቀ የመጠቀ ባለም የታወቀ ማነው ያወቀ የረቀቀ ሁሌ የተደነቀ ማነው የፀና ያልወደቀ ያለ እንደደመቀ በትረ መንግስቱን ያለቀቀ ዘመኑ ያላለቀ እናገራለሁኝ እግዚአብሔር ነው ብዬ እመሰክራለሁ እግዚአብሔር ነው ብዬ በግምት አይደለም ምናገረው ሁሉን ቻይነቱን ስለማውቀው ነው
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection