Song Lyrics

ሳንኳኳ

ሳንኳኳ ሰማይን ስጠብቅ ጌታዬን በድንገት ደረሰልኝ ፀሎቴን መለሰልኝ ባንድ ቃል በሁለት ፊደል እግዚአብሔር በቃ ብሏል ገላገለኝ ከመከራው ብዛት ገላገለኝ ከሚያስጨንቀኝ ገላገለኝ ወደፊት እንዳልሄድ ገላገለኝ ከሚጎትተኝ ችግሬን ጣልክልኝ ወደኋላ ጉልበቴ እንዳይደክም እንዳይላላ ምን እሰጥሃለሁ መዳኒቴ ደስታና ዝማሬ ሞላ ቤቴ ባንድ ቃል በሁለት ፊደል እግዚአብሔር በቃ ብሏል ገላገለኝ በመገላገያው ገላገለኝ እስከመጨረሻው ገላገለኝ ዛሬ የማየውን ገላገለኝ ደግሜ እንዳላየው ሀጥያቴን ጣልክልኝ ወደኋላ ጉልበቴ እንዳይደክም እንዳይላላ ምን እሰጥሃለሁ መዳኒቴ ደስታና ዝማሬ ገባ ቤቴ ደስታዬ ሙሉ ነው ሌላ አያሻኝም በብርና በወርቅ ከቶ አይተካም ፀጋና ሰላሜን አብዝቶ በሂወቴ ሁሌ ደስ ይለኛል ኢየሱስ ገብቶ ቤቴ እኔ ደስ ብሎኛል ኢየሱስ ገብቶ ቤቴ በጣም ደስ ብሎኛል ገብቶልኝ በቤቴ ደስታና ዝማሬ ገባ ቤቴ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection