Song Lyrics

የልቤ አምላክ

Yelibe Amlak

Kalkidan (Lili) Tilahun
Yitayegnal Bizu Neger
አዝ፦ የልቤ አምላክ የልቤ ተባረክ ሆሆ የልቤ አምላክ ተባረክ ሆሆ (፪x) እንደ ጥል ሆንክልኝ እንደ አበባ አበብኩኝ እንደ ሊባኖስ ስሬ በቤትህ ሥር ሰደድኩኝ እንደ ወይራ ውበት እንደ መዓዛዉ በእኔ ያስቀመጥከው ዓለምን ሞላዉ (፪x) አዝ፦ የልቤ አምላክ የልቤ ተባረክ ሆሆ የልቤ አምላክ ተባረክ ሆሆ (፪x) እንደ ዘንባባ ዛፍ እያሳደገኝ ፍሬዬንአበዛው አለመለመኝ እንደ ረካች ገነት አምላኬ አደረገኝ በብዛት በብዛት በብዛት ባርኮኝ አዝ፦ የልቤ አምላክ የልቤ ተባረክ ሆሆ የልቤ አምላክ ተባረክ ሆሆ (፪x) እንደ ጠዋት ፀሐይ እንደሚያበራዉ የጻድቃንም መንገድ እንደዚሁ ነዉ ሙሉ ቀን እስኪሆን ገና ይጨምራል የእኔም ዕድል ፈንታ እነሆ እንዲህ ሆኗል አዝ፦ የልቤ አምላክ የልቤ ተባረክ ሆሆ የልቤ አምላክ ተባረክ ሆሆ (፪x) በውኑ ለእግዚአብሔር የሚሳነው አለ ወይ የሥጋ ለባሽ አምላክ የሚያቅተው አለ ወይ (፪x) ልቤ በእግዚአብሔር ጸና (፬x) እርሱን ተማመነ ሆሆ እርሱን ተማመነ (፪x) በውሃው ላይ እየተረማመደ እየተረማመደ ለሚፈሩ እምነትን አስለመደ (፪x) ማዕበሉም ወጀቡም የሚታዘዝለት ይሄ ማነው የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ነው (፪x) አዝ፦ የልቤ አምላክ የልቤ ተባረክ ሆሆ የልቤ አምላክ ተባረክ ሆሆ (፬x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection